የሕብረት ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች 22 መደበኛ ጠቅላላ ስብሰባ ሕዳር 11 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ስለሚካሄድ የባንኩ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በስብሰባው ላይ እንዲገኙ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የስብሰባው አጀንዳዎች

1.   የስብሰባውን አጀንዳ ማፅደቅ፣

2.   የአክሲዮን ዝውውር ማጽደቅ፣

3.   የዲሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማድመጥ፣ መመርመርና ተወያይቶ ማጽደቅ፣

4.   የኦዲተሮችን ሪፖርት ማድመጥና የባንኩን

-    የሀብትና ዕዳ ሚዛን እና

-    የትርፍና ኪሳራ መግለጫ ማድመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፣

5.   የባንኩን ዓመታዊ የትርፍ ክፍፍል መወሰን፣

6.   የዲሬክተሮች የቦርድ አባላትን የአገልግሎት ክፍያ መወሰን፣

7.   የአገልግሎት ጊዜያቸውን ባጠናቀቁ የቦርድ አባላት ምትክ ምርጫ ማካሄድ

8.   የስብሰባውን ቃለጉባኤ ማጽደቅ

ማሳሰቢያ፡-

§   በስብሰባው ላይ ለመገኘት የማይችል ባለአክሲዮን ከስብሰባው ዕለት ቢያንስ ከሦስት ቀናት በፊት ባንኩ ያዘጋጀውን የውክልና መስጫ ሰነድ በባንኩ ዋና መ/ቤት (በቅሎ ቤት ሜክዎር ኘላዛ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ የባንኩ አክሲዮን ክፍል) ድረስ ቀርቦ በመፈረም ሌላ ሰው ለመወከል ይችላል፡፡

§   ማንኛውም ባለአክሲዮን ለስብሰባው ሲመጣ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው መሆኑን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ዋናውንና አንድ ኮፒ ይዞ መምጣት ይኖርበታል፡፡

§   በውል አዋዋይ የተረጋገጠና በስብሰባው በመካፈል ድምፅ ለመስጠት ግልጽ ስልጣን የሚሰጥ የውክልና ማስረጃ የያዘ ተወካይ በዕለቱ ውክልናውን ይዞ በመቅረብ በስብሰባው ለመሳተፍ ይችላል፡፡ 

የሕብረት ባንክ አ.ማ.

የዲሬክተሮች ቦርድ