ባንካችን የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማዘመን እንዲረዳው ሲጠቀምበት የቆየውን የባንኪንግ ሲስተም የማሻሻል ሥራ (System Upgrade) አንዱ አካል የሆነውን የዳታ ማይግሬሽን ከመጋቢት 20 እስከ 22፣ 2012 ዓ.ም. ባሉት ቀናት ውስጥ ያከናውናል፡፡

በመሆኑም በተጠቀሱት ቀናት በሁሉም ቅርንጫፎቻችን የሒልተን ቅርንጫፍን ጨምሮ እንዲሁም በኦንላይን፣ በሞባይል፣ በኤቲኤም እና በፖስ ማሽኖች ጭምር አገልግሎት የማንሰጥ መሆኑን እያሳወቅን ለሚፈጠረው የአገልግሎት መቋረጥ ከወዲሁ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ hashtag#በሕብረትእንደግ!