ሕብረት ባንክ በራሱ የአይቲ ቡድን አዲሱን / latest version/ የኮር ባንኪንግ ሲስተምና የኦን ላይን ባንኪንግ ፕላትፎርም ሙሉ በሙሉ በመተግበር በሀገራችን የመጀመሪያው ባንክ ሆኗል፡፡ ይህ ስኬት በአፍሪካ ባንኮች ደረጃም ልዩና ያልተለመደ ሊባል የሚችል ነው፡፡ የዚህ ሲስተም ትግበራ ፕሮጀክት የኮር ባንኪንግ ኮንቬንሽናል፣ የኮር ባንኪንግ ኢዝላሚክ፣ የብድር ኦሪጅኔሽንና የኢንተርኔት ባንኪንግ (ኦራክል ዲጂታል ኤክስፒሪያንስ - ኦዲቢኤክስ) አገልግሎቶችን ወደ አዲስ የልህቀት ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው፡፡ ይህ የሚያኮራ ሀገር በቀል ብቃት ባንካችንን ቢያንስ ቢያንስ 7ዐዐ እስከ 8ዐዐ ሺህ ዶላር ወይም በብር ሲሰላ 25 እስከ 26 ሚሊዮን ብር ከሚገመት ወጪ አድኖታል፡፡

 

ሕብረት ባንክ መጋቢት 23/2012 ጀምሮ አዲሱን የኦራክል ሲስተም (ፍሌክስኩዩብ እና ኦዲቢኤክስ ቨርዥን 14.3) በመተግበር አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡፡ ይህ ሲስተም ከአንድ ሚሊዮን በላይ ለሆኑት የባንኩ ደንበኞች አዲስና የላቀ የኦንላይን ባንኪንግ አገልግሎት የሚሰጥ ነው፡፡ በተጨማሪም 315 በላይ የሆኑት የባንኩ ቅርንጫፎች በአዲሱ ሲስተም በመታገዛቸው የባንክ አገልግሎታችንን በላቀ ብቃትና ቅልጥፍና ለመስጠት ያስችለናል፡፡

 

አሁንም ሕብረት ባንክ ደንበኞቹን ወደባንክ መምጣት ሳያስፈልጋቸው በኤሌክትሮኒክ የባንክ አገልግሎት በመጠቀም የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት በጋራ እንድናግዝ አደራ ይላል፡፡

 

ስንተባበር ለችግሮቻችን መፍቻ መላ አናጣም!

 

በሕብረት ሠርተን፣ በሕብረት እንደግ!