ሕብረት ባንክ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የበኩሉን ማድረግ ቀጥሏል፡፡ለዚህም በባንኩ ሥራ አስፈፃሚ የሚመራ ግብረ-ኋይል መቋቋሙ የሚታወስ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ግብረ-ኋይሉ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሙሉ ድጋፍ ሳይለየው ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር በመሥራትየቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እንዲሁም የንግዱን ዘርፍ ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶችን ለመደገፍ እየሠራ ይገኛል፡፡

መንግስት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሚያደርገውን ጥረት ለመደገፍም የባንኩ አስተዳደርናየዳይሬክተሮች ቦርድ በወሰኑት መሠረት ሕብረት ባንክ የብር አምስት ሚሊየን /5,000,000.00 / ድጋፍ ለጤና ሚኒስትር ሰጥቷል፡፡ በቀጣይም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በሚደረጉ ማናቸውም ጥረቶች የበኩሉን ለመወጣት ያለውን ቁርጠኝነት ይገልፃል፡፡

በዚህ አጋጣሚ ሕብረት ባንክ ደንበኞቹ ወደ ባንክ መምጣት ሳያስፈልጋቸው ባሉበት በኤሌክትሮኒክ ባንኪንግ / በሞባይል እና በኦንላይ ባንኪንግ/ እንዲገለገሉ ከዚህ ቀደም ያስተላለፈውን መልዕክት ልብ እንዲሉለት አደራ ይላል፡፡ እነኚህ የሕብረት ባንክ ኤሌክትሮኒክ አገልግሎቶች የባንክ መረጃ ለማየት ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ክፍያዎችን ለመፈጸምና ገንዘብ ለማዘዋወርም ያስችላሉ፡፡ በባንካችን ኦንላይን አገልግሎት በሌሎች ባንኮች ወደሚገኙ የሂሳብ ቁጥሮች ሳይቀር ገንዘብ ማዘዋወር ይቻላል፡፡ የባንኩ ደንበኞች በኦንላይንም ሆነ በሞባይል ባንኪንግ ሲጠቀሙ ምንም አይነት የአገልግሎት ክፍያ አይጠየቁም፡፡በዚህ አኳያ ደንበኞች ያላቸውን ጥያቄ ወደ +251 – 115 573527 በመደወል ማቅረብና መስተናገድ ይችላሉ፡፡

እኛ ኢትዮጵያውያን ተባብረን ከቆምን የማናሸንፈው ፈተና የለም! ለዚህም ታሪክ ምስክር ነው፡፡

ማህረሰባዊ ርቀታችንን በመጠበቅ ለሰዎች ደህንነት እንቁም፡፡ በአሁኑ ወቅት ለወገናችን ያለንን ፍቅር የምንገልፀው የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለማስቆም ማድረግ ያለብንን ጥንቃቄ በመተግበር ነው፡፡

 

በሕብረት፣ እንበልጽግ!