በግል ፈቃደኝነት የተነሳሱ የባንካችን የሥራ አመራሮችና ሠራተኞች የአንድ ወር ሙሉ ደሞዛቸውን በማዋጣት የ836,990 (ስምንት መቶ ሰላሳ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና) ብር በማሰባሰብ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በመንግስት በኩል በተከፈተው የባንኩ የሂሳብ ቁጥር አስገብተዋል፡፡
ሕብረት ባንክ እንደባንክ የራሱን ሀላፊነት በመወጣት እንደሚቀጥል ሁሉ የባንኩ ሠራተኞችም በገንዘብ ብቻ ሳይሆን ደንበኞችን በትጋት በማገልገል፣ ለጤና ቅድምያ የሚሰጥ የአገልግሎት መስጫ አካባቢን በመፍጠር ብሎም ስለቫይረሱ ግንዛቤን በመፍጠር እና በአስፈላጊው ሁሉ ከሕብረተሰቡና ከመንግስት ጐን ለመቆም ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል፡፡
የሕብረት ባንክ ሠራተኞች ለክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች በሙሉ መልካም የፋሲካ በዓል እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል፡፡
ፈጣሪኢትዮጵያንይባርክ!
በሕብረትእንደግ!