Print 

‹‹እልፍ ቅርንጫፍ በሁሉ ደጃፍ››

ሕብረት ባንክ አ.ማ. የወኪል የባንክ አገልግሎት ለመስጠት በብሔራዊ ባንክ በኩል የተቀመጡ አስፈላጊ የሆኑ ዝርዝር ቅድመ ሁኔታዎችን በሙሉ በማሟላት ከህዳር 22 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በሙከራ ደረጃ አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ ይህንን ተከትሎ በሙከራ ወቅት በባንኩ የተመዘገበውን አጥጋቢ ውጤት በቅርበት የቃኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አገልግሎቱን በይፋ ለመስጠት የሚያስችለውን ፍቃድ መጋቢት 22 ቀን 2007 ዓ.ም ለባንኩ ሰጥቷል፡፡

ባንካችን ይህን የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ሲነሳ በዋናነት መሠረት ያደረገው በመደበኛ የባንኩ ቅርንጫፎች አገልግሎት ለማግኘት ተደራሽ ባልሆነባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ሲሆን፤ በዚህ መልኩ በተለያየ ቦታ ተሰባጥረው የሚገኙ ተጠቃሚዎችን ቀላልና አመቺ በሆነ ሁኔታ መሠረታዊ የሆኑ የባንክ አገልግሎት አይነቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል በማሰብ ይህን አገልግሎት ለገበያ አቅርቧል፡፡

በዚህም መሠረት ባንካችን የሙከራ አገልግሎት ለመሥጠት ፍቃድ ካገኘበት ሕዳር 22 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በርካታ ተግባራት የተሰሩ ሲሆን፤ እስካሁንም ቁጥራቸው 85 የሚደርሱና በተለያየ የአገልግሎተ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ለአብነትም መድሃኒት ቤቶች# ካፌዎች# ሆቴሎች# ነዳጅ ማደያዎች# የልብስ መሸጫ መደብሮች# አስጎብኝ ድርጅቶች እና መሰል ተቋማት የባንካችን ወኪል በመሆን የሕብር ወኪል የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል 70 የሚሆኑት ወኪል ድርጅቶች ከአዲስ አበባ ውጪ በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ሲሆን፤ 15 የሚሆኑት ደግሞ በአዲስ አበባ ውስጥ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

ሕብር ወኪል የባንክ አገልግሎትን በመጠቀም ሒሳብ መክፈት# ገንዘብ ገቢና ወጪ ማድረግ# ገንዘብ ማስተላለፍ# ገንዘብ ከኤም ዋሌት ወደ ባንክ ሒሳብ ወይም ከባንክ ወደ ኤም ዋሌት ሒሳብ ማስተላለፍ እንዲሁም ገንዘብ መላክና መቀበልን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶች እየተሰጡ ይገኛል፡፡

በሕብር ወኪል የባንክ አገልግሎት የሚሠጡትን እንዚህን አገልግሎቶች ደንበኞች በሞባይል ስልካቸው በመጠቀምና ወደ *885#በመደወል ወይም በኢንተርኔት www.unitedagent.com.et በመጠቀም ገንዘብ ማስተላለፍን ጨምሮ ከሒሳባቸው ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የተለያዩ መረጀዎች ማግኘት ይችላሉ፡፡

የሕብር ወኪል የባንክ አገልግሎት ደንበኞች ካለስጋት በአገልግሎቱ እንዲጠቀሙ የሚያስችላቸውን የደህንነት ሁኔታ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲያካትት የተደረገ ሲሆን፤ ከዚህም ባሻገር ለደንበኞች አጠቃቀም እጅግ ቀላልና አመቺ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም ደንበኞች በአገልግሎት አሠጣጥ ዙሪያ ሊያነሱ የሚችሏቸውን የተለያዩ ጥያቄዎች በ995 ላይ በመደወል ፈጣን ምላሽ ማግኘት የሚችሉበትን አሰራር ዘርግቷል፡፡