ሕብረት ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና ተበዳሪዎች በገቡት ውል መሠረት ብድሩን ወቅቱን ጠብቀው ባለመክፈላቸው ምክንያት የተረከባቸውን እና ከዚህ በታችየተመለከቱትን ንብረቶች በዝግ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡

ስለዚህ

 

  1. ንብረቶቹን ለማየት የሚፈልጉ በሚያመቻቸው ጊዜ ከላይ በሠንጠረዡ በተገለጹት አድራሻዎች ዘወትር ሰኞ፣ረዕቡ እና ዓርብ በሥራ ሰዓት ጠዋት  ከ3፡00- 6፡00 ከሰዓት ከ 8፡00-10፡00 ሰዓት በመገኘት ንብረቶቹን ማየት ይቻላል፡፡
  2. የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ወይንም 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ /ሲ.ፒ.ኦ/ በማቅረብ መወዳደር ይቻላል፡፡
  3. አሸናፊየሚሆነውተጫራችያሸነፈበትንገንዘብ በ15/አስራ አምስት/ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፤ባይከፍል ግን ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ የማይመለስለት ሲሆን  ሆኖም ጨረታውን ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ገንዘብ አሸናፊው ከተለየ በኋላ ይመለስላቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ሚክዎር ፕላዛ ሕንፃ ምድር ቤት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2010 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል፡፡
  5. ጨረታው ጥቅምት 20 ቀን 2010 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት  ተዘግቶ በማግስቱ ጥቅምት 21 ቀን 2010 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በዋናው መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ የቦርድ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. ንብረቶቹን በገዥው ስም ለማዛወር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ማረጋገጫ ይጽፋል፡፡
  7. ንብረቶቹን ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ከፍለው ለሚገዙ ባንኩ ቅድሚያ የሚሰጥ ቢሆንም እንዳስፈላጊነቱ ከባንኩ ጋር በመደራደር በባንኩ የብድር ፖሊሲ መሠረት ንብረቶቹን በብድር ለመግዛት ለሚፈልጉም የእያንዳንዱ ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 50% ድረስ ብድር ሊመቻች ይችላል፡፡ ሆኖም  ብድር ለመጠየቅ የሚፈልጉ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ከማስገቢያው 3/ሶስት/ቀናት በፊት ማለትም ከጥቀምት 17 ቀን 2010 ዓ.ም. በፊት የብድር ጥያቄያቸውን ለሚመለከተው የስራ ክፍል በማቅረብ ብድር ለማግኘት የሚችሉ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮችን ገዥው/ አሸናፊው ይከፍላል፡፡
  9. ለበለጠ ማብራሪያ ሕብረት ባንክ አ.ማ ዋናው መስሪያ ቤት በስልክ ቁጥር 0114-655222 በውስጥ ቁጥር 250 ወይም 299 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  10. ባንኩ ንብረቶቹን ለመሸጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ሕብረት ባንክ አ.ማ