አብረን ተጉዘናል፤ ሃያ ዓመታት !

ሃያ ክረምት አልፎ ፤...ሃያ መስከረም ሲጠባ ፤

ከናንተ ጋር ... ዘመን ቀይረና ል ፤
ሃያ ጊዜ ፤ አዲስ አደይ አበባን ፤
ሃያ ጊዜ ፤ አዲስ የመስቀል ወፍ ስትመጣ አይተናል ፤
ሃያ ዓመታትን ፤ ወንዞቻችን ፤ ከዘመን ጋር ሲሞሸሩ ፤
መስኩ ... በአደይ ሲያሸበርቅ ፤

አዲስ ዓመት፤ ... አዲስ በዓል ፤... አዲስ ምድር ፤ 
... አዲስ ተስፋ ፤ ሕብረት ሲፈጥሩ ፤ ... ሕብረት ባንክ ፤
ሃያ ዓመታትን ፤

... መተሳሰብ ፤ መነፋፈቅ ፤ መደጋገፍ ፤ መጠያየቅ ፤
ሕብር ሆነው ፤ ሲያንፀባርቁ ፤ ... ሕብረት ባንክ ነበር !
እንኳን አደረሳችሁ !!!

አነሆ ፤ በፍቅር እንድንቀበል ፤ ከውጭ አገር ፤ለበዓል ማድመቂያ ፤

በዌስተርን ዩኒየን ፤ በደሀብሽል ፤ ... በመኒግራም፤ በኤክስፕረስ መኒ ፤

በወርልድ ሪሚትና በሌሎችም ገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በኩል፤ የተላከሎትን ገንዘብ ፤

ከወዳጆ ወደ እጆ ሊያቀብል ፤ ሕብረት ባንክ፤ ዛሬም ከርሶ ጋር ነው !

... በባንካችን የስዊፍት ኮድ በኩል የተላኮለትን
ገንዘብም ፤ ... በአቅራቢያዎ ከሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ ፤ በፍጥነት መቀበል ስለሚችሉ ፤ ደስ ይለናል !

 

መልካም አዲስ ዓመት !!!

 

ሕብረት ባንክ !!!!
በሕብረት ሰርተን ፤ በሕብረት እንደግ !!!!

 

>> አብረን ተጉዘናል !

ሃያ ዓመታት ፣ ... እንደዘበት እብስ ሲሉ ፤
ሕብረት ባንክ ፤ ... ሕብረትን ጠነሰስንበት ፤
እያንዳንዱን ቀን ... አንድነትን ዘመርንበት !
ስምን ከግብር አስማምተን ፤
ከአድማስ አድማስ ተጓዝንበት !

ሃያ ዓመታት !
የስኬት ጉዞ ከሕብረት ባንክ ጋር!
ሕብረት ሕብረትን የሚሉ ፤ ብዙ ምሰሶዎችን ተክለናል !
እኒህ ዓመታት ፣ አብረን ሰርተን ፤ ... አብረን ያደግንባቸው ናቸው !
ሕብረት ማለት ፣ ... ብዙ አንዳንዶች ያሉበት ፤
የአንድነት ፣ የሥራና የስኬት መሠረት ነው !

የኛ ውበት ፣ ... የኛ እውነት መሠረቱ ፤ ሕብረቱ ነው ... አንድነቱ !
ከዘመን ጋር ዘመናዊነትን ፤
ከፍቅር ጋር አክብሮትን ፤ ከትጋት ጋር ፣ ዕድገትና ስኬትን አስማምተን ፤
ሃያ ዓመታት ... ፣ ... አብረን ተጉዘናል !

ሕብረት ባንክ ! 
በሕብረት ሰርተን ፣ በሕብረት እንደግ !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር SBB/62/2015 መሠረት የሕብረት ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች ባካሄዱት 19ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ መምረጣቸው ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሠረት ኮሚቴው ዕጩዎችን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጅቱን ስላጠናቀቀ የዳይሬክተሮች ቦርድ ዕጩ አባላትን ጥቆማ እስከ ጳጉሜ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ ብቻ ስለሚቀበል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/54/2012 እና SBB/62/2015 ላይ የተዘረዘሩት የሚከተሉት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ዕጩዎችን ከጊዜ ገደቡ በፊት እንድትጠቁሙ ለመላው የባንካችን ባለአክሲዮኖች ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

1.   የባንኩ ባለአክሲዮን የሆነና የቦርድ አባል ሆኖ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ፣

2.   ዕድሜው 30 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ፣

3.   በማንኛውም ባንክ ሠራተኛ ያልሆነ፣

4.   ሀቀኛ፣ ታማኝ እና መልካም ዝና ያለው በተለይም በማጭበርበር፣ እምነት በማጉደል፣ ትክክለኛ ያልሆነ የሂሳብ መግለጫ በማቅረብና በመሳሰሉት ተከስሶ በፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶበት የማያውቅ፣

5.   በሌላ የፋይናንስ ድርጅት የቦርድ አባል ወይም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ያልሆነ፣

6.   በራሱ ወይም በሚመራው ወይም ዳይሬክተር በሆነበት ድርጅት ላይ የመክሰር ክስ ያልቀረበበት ወይም የኪሳራ ውሳኔ ያልተሰጠበት፣

7.   በኪሳራ ምክንያት ንብረቱ ለዕዳ ማቻቻያነት ያልተወሰደበት፣

8.   የባንክ ብድር ባለመክፈሉ ምክንያት ንብረቱ በሐራጅ ያልተሸጠ፣ ተከሶ ያልተፈረደበት ወይም እሱ የሚመራው ወይም ዳይሬክተር የሆነበት ድርጅት ከገንዘብ ተቋማት የተበደረውን ገንዘብ ባለመክፈሉ ብድሩ ወደ ጤናማ ያልሆነ የብድር ደረጃ ያልዞረበት/ያልገባበት (NPL ያልሆነበት)፣

9.   በቂ ስንቅ/ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ሰጥቶ ሂሳቡ ያልተዘጋበት፣

10.ታክስ ባለመክፈል ተከሶ ጥፋተኛ ያልተባለ፣

11.ከሚመረጡት የቦርድ አባላት መካከል ሰባ አምስት በመቶ (75%) የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ከዚያ በላይ ሊኖራቸው የሚገባ ሲሆን በባንክ፣ በፋይናንስ፣ በኢኮኖሚክስ፣ በአካውንቲንግ፣ በሕግ፣ በንግድ ስራ አስተዳደር፣ በኦዲት፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና በኢንቨስትመንት የሙያና የስራ ዘርፎች ልምድ ያለው ቢሆን ይመረጣል፡፡ የተቀሩት ሃያ አምስት ከመቶ (25%) ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ መሆን አለባቸው፡፡

12.በተጨማሪም መመሪያዎቹ ላይ የተገለጹት ሌሎች መመዘኛዎችን የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡

ማሳሰቢያ፣

1.   በተባዕታይ ፆታ የተገለፀው ለአነስታይ ፆታም ያገለግላል፡፡

2.   ጥቆማውን

·       በሕብረት ባንክ አ.ማ. ዋና መስሪያ ቤት በቅሎ ቤት ቅርንጫፍ ሜክዎር ኘላዛ ሕንጻ 1ኛ ፎቅ በባንኩ ፕሬዚደንት ቢሮ ውስጥ በሚዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በአካል ቀርቦ በማስገባት ወይም

·       በመልዕክት ሳጥን ቁጥር 19963 ሕብረት ባንክ አ.ማ.  ለዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ጽ/ቤት፤ አዲስ አበባ በሚል በመላክ ወይም

·       በኢ-ሜይል ሲላክ  This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  በመላክ፡፡ ኢ-ሜይል ሲላክ ፎርሙን ሞልቶ ስካን አድርጎ መላክ አለበት፡፡

3.   የጥቆማ ማቅረቢያ ፎርሙ ለባንኩ ባለአክሲዮኖች በአክሲዮን ግዢ ጊዜ ባስመዘገቡት የፖስታ አድራሻ የሚላክ ሲሆን በተጨማሪም ከባንኩ ዋና መ/ቤት ፋይናንስ እና አካውንትስ መምሪያ፣ ከባንኩ ቅርንጫፎች ወይም ከባንኩ ድረ-ገጽ www.unitedbank.com.et/Form ማግኘት ይቻላል፡፡

4.   ለተጨማሪ ጥያቄ፤ ጥቆማ እና አስተያየት ፋይናንስ እና አካውንትስ መምሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-416-9580 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

5.   ከጳጉሜ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀኑ 6፡00 ሰዓት በኃላ የሚቀርቡ ጥቆማዎች  ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑን ከወዲሁ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

6.   ተጠቋሚው የአስመራጭ ኮሚቴ አባል ያልሆነ መሆን አለበት፡፡

 

የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ

 

 

ሕብረት ባንክ አ.ማ.

United Bank collaborating with Ethiopian Airlines in the E-Commerce dynamism
United Bank, a partner with Ethiopian in facilitating E-commerce (payment) to e-tickets sales embarked on a new payment development that took the existing service of selling the airlines e-tickets on the Bank’s digital platform to a new and higher level.
As a result, the e-ticket selling process now enables customers to book and effect payment via a Straight Through Processing (STP) interfacing. The new enhanced system has upgraded new features that automatically interfaced with Ethiopian e-ticketing system. Accordingly, when a customer books at Ethiopian by using ET Mobile App (that can be downloaded from play or apple store); the reservation will hit the bank’s system instantly. Later, when customer pays using United Bank’s multi channel services (i.e. Pay@Mobile, Pay@Internet, Pay@Branches, etc.), Ethiopian Airlines will be notified right away on payment confirmation and then the eticket will be issued by Ethiopian to the customer.
This digital payment system offers a one-point solution for all e-ticket needs of passengers i.e. whether the customer reserves its seat via telephone (using Ethiopian Airlines Global Call Center – GCC) or Ethiopian Airlines Mobile APP. Individuals and businesses will profit from this unique and convenient service that saves time and cost.
United Bank is a share company that stands among the few prominent private Banks in Ethiopia, operating all over the country with more than 230 branches. United Bank provides an array of banking services that include: conventional, interest free and multi-Channel banking products through various service channels that include Agency Banking, ATMs, POS, Internet banking and Mobile.
United is proud to be a partner with the nation’s flag carrier to serve the wider population through convenient payment system.