የሕብረት ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች ሕዳር 9 ቀን 2008 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል ባካሄዱት 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር SBB/62/2015 መሰረት የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባላትን የመረጡ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ኮሚቴውም ባለአክሲዮኖች ጥቆማ እንዲያደርጉ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ባሳወቀው መሰረት ጥቆማዎችን ሲቀበል ቆይቷል፡፡ የጥቆማ ማቅረቢያው ጊዜ ተጠናቋል፡፡ ስለሆነም አስመራጭ ኮሚቴው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወጣው መመሪያ ቁጥር SBB /62/2015 አንቀጽ 8.2.4 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በባለአክሲዮኖች ከተጠቆሙት  መሀል ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት የተቀመጡትን መመዘኛዎችን ያሟላሉ ብሎ ያመነባቸውን ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ዕጩዎችን ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት ምርጫ  በዕጩነት ያቀረበ መሆኑን ያሳውቃል፡፡

1.  አቶ ኤፍሬም ኃ/ማርያም በዛብህ

2.  አቶ ውቤ ክንፈ ወ/ፃድቅ

3.  ወ/ሮ አዛለች ይርጉ በላይነህ

4.  ወ/ሮ አፀደወይን ተክሌ ሪጆ

5.  አቶ በላይ ከበደ ዓለሙ

6.  አቶ ሰለሞን ከበደ ኃይሌ

7.  አቶ ስለሺ ደበበ ወዳጄ

8.  አቶ ብርሃኔ ካህሣይ ተወልደ

 ሕብረት ባንክ አ.ማ.

 የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ