የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር SBB/62/2015 መሠረት የሕብረት ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች ባካሄዱት 19ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ መምረጣቸው ይታወሳል፡፡

በዚሁ መሠረት ኮሚቴው ዕጩዎችን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጅቱን ስላጠናቀቀ የዳይሬክተሮች ቦርድ ዕጩ አባላትን ጥቆማ እስከ ጳጉሜ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ ብቻ ስለሚቀበል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/54/2012 እና SBB/62/2015 ላይ የተዘረዘሩት የሚከተሉት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ዕጩዎችን ከጊዜ ገደቡ በፊት እንድትጠቁሙ ለመላው የባንካችን ባለአክሲዮኖች ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

1.   የባንኩ ባለአክሲዮን የሆነና የቦርድ አባል ሆኖ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ፣

2.   ዕድሜው 30 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ፣

3.   በማንኛውም ባንክ ሠራተኛ ያልሆነ፣

4.   ሀቀኛ፣ ታማኝ እና መልካም ዝና ያለው በተለይም በማጭበርበር፣ እምነት በማጉደል፣ ትክክለኛ ያልሆነ የሂሳብ መግለጫ በማቅረብና በመሳሰሉት ተከስሶ በፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶበት የማያውቅ፣

5.   በሌላ የፋይናንስ ድርጅት የቦርድ አባል ወይም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ያልሆነ፣

6.   በራሱ ወይም በሚመራው ወይም ዳይሬክተር በሆነበት ድርጅት ላይ የመክሰር ክስ ያልቀረበበት ወይም የኪሳራ ውሳኔ ያልተሰጠበት፣

7.   በኪሳራ ምክንያት ንብረቱ ለዕዳ ማቻቻያነት ያልተወሰደበት፣

8.   የባንክ ብድር ባለመክፈሉ ምክንያት ንብረቱ በሐራጅ ያልተሸጠ፣ ተከሶ ያልተፈረደበት ወይም እሱ የሚመራው ወይም ዳይሬክተር የሆነበት ድርጅት ከገንዘብ ተቋማት የተበደረውን ገንዘብ ባለመክፈሉ ብድሩ ወደ ጤናማ ያልሆነ የብድር ደረጃ ያልዞረበት/ያልገባበት (NPL ያልሆነበት)፣

9.   በቂ ስንቅ/ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ሰጥቶ ሂሳቡ ያልተዘጋበት፣

10.ታክስ ባለመክፈል ተከሶ ጥፋተኛ ያልተባለ፣

11.ከሚመረጡት የቦርድ አባላት መካከል ሰባ አምስት በመቶ (75%) የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ከዚያ በላይ ሊኖራቸው የሚገባ ሲሆን በባንክ፣ በፋይናንስ፣ በኢኮኖሚክስ፣ በአካውንቲንግ፣ በሕግ፣ በንግድ ስራ አስተዳደር፣ በኦዲት፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና በኢንቨስትመንት የሙያና የስራ ዘርፎች ልምድ ያለው ቢሆን ይመረጣል፡፡ የተቀሩት ሃያ አምስት ከመቶ (25%) ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ መሆን አለባቸው፡፡

12.በተጨማሪም መመሪያዎቹ ላይ የተገለጹት ሌሎች መመዘኛዎችን የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡

ማሳሰቢያ፣

1.   በተባዕታይ ፆታ የተገለፀው ለአነስታይ ፆታም ያገለግላል፡፡

2.   ጥቆማውን

·       በሕብረት ባንክ አ.ማ. ዋና መስሪያ ቤት በቅሎ ቤት ቅርንጫፍ ሜክዎር ኘላዛ ሕንጻ 1ኛ ፎቅ በባንኩ ፕሬዚደንት ቢሮ ውስጥ በሚዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በአካል ቀርቦ በማስገባት ወይም

·       በመልዕክት ሳጥን ቁጥር 19963 ሕብረት ባንክ አ.ማ.  ለዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ጽ/ቤት፤ አዲስ አበባ በሚል በመላክ ወይም

·       በኢ-ሜይል ሲላክ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. በመላክ፡፡ ኢ-ሜይል ሲላክ ፎርሙን ሞልቶ ስካን አድርጎ መላክ አለበት፡፡

3.   የጥቆማ ማቅረቢያ ፎርሙ ለባንኩ ባለአክሲዮኖች በአክሲዮን ግዢ ጊዜ ባስመዘገቡት የፖስታ አድራሻ የሚላክ ሲሆን በተጨማሪም ከባንኩ ዋና መ/ቤት ፋይናንስ እና አካውንትስ መምሪያ፣ ከባንኩ ቅርንጫፎች ወይም ከባንኩ ድረ-ገጽ www.unitedbank.com.et/Form ማግኘት ይቻላል፡፡

4.   ለተጨማሪ ጥያቄ፤ ጥቆማ እና አስተያየት ፋይናንስ እና አካውንትስ መምሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-416-9580 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

5.   ከጳጉሜ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀኑ 6፡00 ሰዓት በኃላ የሚቀርቡ ጥቆማዎች  ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑን ከወዲሁ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

6.   ተጠቋሚው የአስመራጭ ኮሚቴ አባል ያልሆነ መሆን አለበት፡፡

 

የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ

ሕብረት ባንክ አ.ማ.