በሕብረት ባንክ የኤቲኤም ማሽኖች ገንዘብ ማውጣት ብቻ ሳይሆን መላክም ይችላሉ!
በአገልግሎቱ ለመጠቀም የሚከተለውን ቅደም ተከተል ይከተሉ

1. ገንዘብ ለመላክ

  • ካርድዎን በኤቲኤም ውስጥ ያስገቡ፣
  • የሚስጥር ቁጥርዎን (ፒን) ያስገቡ፣
  • ከተዘረዘሩት የአገልግሎት አይነቶች "ገንዘብ መላክ" ለመላክ የሚለውን ይምረጡ፣
  • ባለ አስር አሃዝ የተቀባይ ማረጋገጫ ቁጥር ያስገቡ (የሚፈልጉትን አስር ቁጥሮች ማስገባት ይችላሉ፡፡ ካስገቡ በኋላ ቁጥሮቹን እንዳይረሱ ጽፈው ይያዙ)፣
  • መላክ የሚፈልጉትን የገንዘብ መጠን ያስገቡ (በቀን እስከ ብር 3,500.00 መላክ ይችላሉ)፣
  • የላኩትን የገንዘብ መጠን እና የሚስጥር ቁጥር የሚገልጽ ደረሰኝ ከኤቲኤም ማሽኑ ላይ ያገኛሉ፣
  • ደረሰኙን እንዳገኙ ለላኩለት ግለሰብ ባለ አስር ቁጥሩን የተቀባይ ማረጋገጫ እና የሚስጥር ቁጥሩን ይንገሩ

2. ገንዘብ ለመቀበል

  • ኤቲኤሙ ላይ "ገንዘብ መቀበል" የሚለውን ይምረጡ፣ ባለ አስር አሃዝ የተቀባይ ማረጋገጫ ቁጥርዎን ያስገቡ፣ የሚስጥር ቁጥርዎን ያስገቡ፣
  • ገንዘብዎን ከኤቲኤም የገንዘብ ማውጫው ላይ ይውሰዱ
  • ገንዘብ ለመቀበል የባንክ ሒሳብ መክፈት ወይም የሕብር ካርድ መያዝ አያስፈልግም፡፡

ማሳሰቢያ፡

 

ገንዘብ መላክም ሆነ መቀበል የሚቻለው የሕብረት ባንክን ኤቲኤም ማሽኖች በመጠቀም ብቻ ነው፡፡