‹‹በሕብረት ባንክ ሁሌም አዲስ ነገር አለ››
እጅግ ዘመናዊ በሆነ የቴክኖሎጂ ማዕቀፍ በመደገፍ በተዘረጉ ዘርፈ ብዙ የአገልግሎት አማራጮች የደንበኞቹን ፍላጎት በተሟላ ሁኔታ ለማርካት ዘወትር የሚተጋው ሕብረት ባንክ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሚደረጉ የውጪም ሆነ የአገር ውስጥ በረራዎች የጉዞ ትኬት ክፍያ በመፈፀም ቲኬት ማግኘት የሚችሉበትን አዲስ የአገልግሎት አማራጭ አቀረበልዎ፡፡
ሕብረት ባንክ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር በጀመረው በዚህ አዲስ እና ዘመናዊ አገልግሎት ተጓዦች አየር መንገዱ በዘረጋው ዓለም አቀፍ የጥሪ ማዕከል (+251 116 65 66 66) ላይ ስልክ በመደወል ላስያዙት የጉዞ ቦታ የትኬት ዋጋ ተመኑን ወደ አየር መንገዱ የትኬት ሽያጭ ቢሮዎች መሄድ ሳያስፈልጋቸው፡-
 
 
 1. ሳምንቱን ሙሉ ለ24 ሰዓታት አገልግሎት በሚሠጠው የሒልተን ቅርንጫፋችን ጨምሮ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በስፋት ተሠራጭተው በሚገኙት የሕብረት ባንክ ቅርንጫፎች በመሄድ ክፍያ በመፈፀም ትኬቱን ማግኘት ይችላሉ፣
 2. በባንኩ የሕብር ሞባይል በመጠቀም እንዲሁም ሕብር ኦንላይን አገልግሎት በመጠቀም ክፍያ መፈፀምና ትኬት
 3. መቁረጥ የሚያስችላቸው ዘመናዊ አገልግሎት ነው፡፡
ይህ አዲስ አገልግሎት በአየር መንገዱ ለሚጓዙ የባንካችን ደንበኞችም ሆነ የሕብረት ባንክ ሒሳብ ለሌላቸው የአገልግሎታችን ተጠቃሚዎች በሙሉ ፍፁም ደኅንነቱ በተጠበቀና አስተማማኝ በሆነ ሁኔታ ጊዜና ገንዘብዎን በመቆጠብ የሚስተናገዱበት እጅግ ዘመናዊ፣ ቀላልና አመቺ የአገልግሎት አማራጭ ነው፡፡

አገልግሎቱን ለማግኘት፡-

 • ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ የጥሪ ማዕከል (+251 116 65 66 66) በመደወል የበረራ ቦታ ማስያዝ፤ ወይም በአየር መንገዱ መረጃ መረብ የበረራ ቦታ ሲያሲዙ (Book) ሲያደርጉ ከታች የተጠቀሱትን መረጃዎች የያዘ አጭር የሞባይል መልዕክት ከአየር መንገዱ የጥሪ ማዕከል ይደርስዎታል፡-
  • በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተያዘ የበረራ ቦታ መለያ ቁጥር፣
  • የተጓዥ ሙሉ ስም፣
  • የዋጋ ተመን
 • ከላይ የተጠቀሰውን መረጃ በመያዝ በአቅራቢያዎ በሚገኝ በማንኛውም የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ክፍያውን በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንኩ ከሚገኝ የሕብረት ባንክ ሒሳብ ላይ ተቀናሽ በማድረግ የትኬት ዋጋ ክፍያውን መፈፀም፡፡ አገልግሎቱን ለማግኘት ምንም አይነት ተጨማሪ ክፍያ መክፈል አይጠበቅም፡፡
እርስዎ የሕብረት ባንክ ደንበኛ ከሆኑና በባንኩ የሕብር ሞባይል ወይም ሕብር ኦንላይን አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑ የእጅ ስልክዎን ብቻ በመጠቀም ወይም የሕብር ኦንላይን አገልግሎት በመጠቀም በየትኛውም ሰዓትና ቦታ የአገልግሎት ክፍያውን በቀጥታ መፈፀም ይችላሉ፡፡
 
 • የጉዞ ትኬት ክፍያውን በሕብረት ባንክ በኩል እንደፈፀሙ ወዲያውኑ የኢትዮጵያ አየር ማንገድ የጉዞ ትኬትዎን በሞባይል መልክት ይልክሎታል፡፡
 • በበረራ ወቅት ከባንኩ የተሰጠዎትን ትኬት በመያዝ በአየር መንገዱ የበረራ ማስተናገጃ በማሳየት በረራውን ማከናወን ይችላሉ፡፡

መልካም ጉዞ !