ሕብረት ባንክ ከብሔራዊ ቲያትር ወደ ሜክሲኮ አደባባይ በሚወስደው የራስ አበበ አረጋይ ጎዳና ከአዲስ አበባ የንግድ ስራ ኮሌጅ ዋና መግቢያ ትይዩ ሊያሰራ ያቀደውን የ32 ፎቅ የዋና መ/ቤት ሕንፃ ለመገንባት ቻይና ጂያንግሱ ኢንተርናሽናል ከተሰኘ የቻይና ኩባንያ ጋር የግንባታ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ግንቦት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል በተከናወነው በዚህ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባንኩን በመወከል የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ታዩ ዲበኩሉ እንዲሁም ቻይና ጂያንግሱ ኢንተርናሽናልን በመወከል በኢትዮጵያ የኩባንያው ሥራ አስኪያጅ ኢንጂኔር ዙ ጃን ኮንትራቱን ፈርመዋል፡፡

እንደሚታወቀው ሕብረት ባንክ ከደረሰበት የእድገት ደረጃ ጋር ተመጣጣኝ የሆነና ለባንኩ ሁለንተናዊ እድገት ትልቅ ሰትራቴጂያዊ ፋይዳ እንደሚያበረክት የታመነበትን የራሱን የዋና መ/ቤት ሕንፃ ከአዲስ አበባ አስተዳደር በተረከበው የ3338 ካሬ ሜትር ቦታ ለመገንባት እቅድ ነድፎ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከጀመረ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

የሕንፃውን አርክቴክቸራል ዲዛይን ለመምረጥ ከዚህ ቀደም በአገራችን እምብዛም ባልተለመደ ሁኔታ በሙያው በአገራችን ውስጥ የካበተ ልምድ ያላቸውን ስመጥር የአርኪቴክቸራል ዲዛይን ባለሙያዎችን በዳኝነት ያካተተ የውድድር ሂደት በማድረግ ከ40 በላይ የሆኑ ተወዳዳሪዎችን ያሳተፈ ውድድር አካሂዷል፡፡ ከፍተኛ ውድድር በታየበት በዚህ ውድድርም 7 ተወዳዳሪዎች ለመጨረሻው ዙር በማለፍ እጅግ ማራኪ የሆኑ ስራዎቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን፤ በመጨረሻም በእስክንድር አርኪቴክትስ የአርክቴክቸራል ኩባንያ የተሰራው የሕንፃ ዲዛይን አሸናፊ ሆኖ ተመርጧል፡፡ ይህንንም ተከትሎ አሸናፊው ድርጅት የሕንፃውን ዲዛይን በተመለከተ ምክር በሚሠጡት ታዋቂ ኢትዮጵያዊ የምህንድስና ባለሙያዎች በመታገዝ የሕንፃውን ዝርዝር ዲዛይን አዘጋጅቶ የግንባታ ሂደቱን በመቆጣጠር ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ በአሁን ወቅትም የሾሪንግና የቁፋሮ ስራ የተጠናቀቀ በመሆኑ በያዝነው ወር ውስጥ የመሠረት ሥራ ይጀመራል፡፡

የግንባታውን ስራ የሚያከናውነው ቻይና ጃንግሱ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያን ጨምሮ ከቻይና ውጪ ባሉት ከ3ዐ በላይ ቅርንጫፎች በርካታ ግንባታዎችን ያከናወነ ኮንትራክተር ነው፡፡

ሕብረት ባንክ የሚያሰራው ይህ እጅግ ዘመናዊ የሆነ የዋና መ/ቤት ሕንፃ ሲጠናቀቅ ከዋናው መ/ቤት ሕንፃ በተጨማሪ የዋና መ/ቤት ቅርንጫፍ# ለባንኩ ሠራተኞች ግልጋሎት የሚሠጥ የመሰብሰቢያ አዳራሽ# የስልጠና ክፍሎች# የሠራተኞች መዝናኛና እስከ 200 መኪናዎችን በአንድ ጊዜ ለማቆም የሚያስችል ከመሬት በታች ያለ ባለ አራት ደርዝ የመኪና ማቆሚያ ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም ከዋና መ/ቤት ቅርንጫፍ በስተግራ በሚገኘው ባለ አራት ፎቅ የሕንፃ ክፍል ለገበያ ማዕከል# ለሱቆችና ለካፊቴሪያ ግልጋሎት የሚሆን ቦታ ይኖረዋል፡፡

የሕብረት ባንክ ዋና መ/ቤት ሕንፃ በአይነቱ ልዩ የሆነ የሕንፃ መቆጣጠሪያ ሲስተም (BMS) የሚኖረው ሲሆን፤ ስምንት ዘመናዊ አሳንሰሮች# የባንክ ሴኩሪቲ ሲስተም እና የዳታ ማዕከልም ይኖሩታል፡፡

 

በሕብረት ሰርተን በሕብረት እንደግ!

United, we prosper!

 For Additional pictures click here 

United Bank has opened its 124th branch in Addis Ababa city by the name of Ferensay Legasion branch.

This new Branch is integrated to the core banking system of the bank, providing a full-fledged modern banking service.

በሕብረት ሰርተን በሕብረት እንደግ!
United, we prosper!
www.unitedbank.com.et

United Bank has opened its 123rd branch in Addis Ababa City by the name of Medhanit branch.

This new Branch is integrated to the core banking system of the bank, providing a full-fledged modern banking service.
በሕብረት ሰርተን በሕብረት እንደግ!

United, we prosper!
www.unitedbank.com.et

United Bank has opened its 122th branch in Awash town by the name of Awash Sebat Kilo branch.

This new Branch is integrated to the core banking system of the bank, providing a full-fledged modern banking service.
በሕብረት ሰርተን በሕብረት እንደግ!

United, we prosper!
www.unitedbank.com.et