ሕብረት ባንክና የሕብረት ባንክ ሠራተኞች ለሜቄዶንያ አረጋውያንና አእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የብር 3.5 ሚሊዮን የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ

በሜቄዶንያ የሕብረት ባንክ ሆኖ የተሰየመው ጳጉሜ 4 ሕብረት ባንክና ሠራተኞቹ ለሜቄዶንያ አረጋውያንና አእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የገንዘብ ስጦታ ጳጉሜን 4 ቀን 2015 ዓ.ም በማዕከሉ በመገኘት የ3,500,000 (ሦስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ) የብር ስጦታን አበርክቷል፡፡

በዕለቱም የሕብረት ባንክ የአመራር አባላት ሕሙማኑንና በመገንባት ላይ የሚገኘውን የማዕከሉን ሕንፃ በመጎብኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውንና አብሮነታቸውን ገልጸዋል፡፡

የሕብረት ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ከበደ በመልዕክታቸው ከ5700 በላይ ሠራተኞቻችንን በመወከል ለአዲሱ ዓመት የእንኳን በሠላም አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን ያሉ ሲሆን የሜቄዶንያ መስራች የሆኑት አቶ ቢኒያም በለጠ በበኩላቸው ሕብረት ባንክ ከዚህ ቀደም ላደረገው ድጋፍና አስተዋፅኦ እንዲሁም ለዛሬውና ለሁልጊዜ ድጋፉ ከልብ አመስግናለሁ ብለዋል፡፡

ሕብረት ባንክ በሜቄዶንያ የሕብረት ቀን ሆኖ በተሰየመው ጳጉሜን 4 በመገኘት የብር ድጋፍ ሲያደርግ ይህ ሁለተኛ ጊዜው ነው፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts