ሕብረት ባንክ ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የኮምፒውተር ድጋፍ አደረገ፡፡
ሕብረት ባንክ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ባንክ ነው፡፡ ይሕንኑ ተግባር አጠናክሮ በመቀጠል ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ 10 (አስር) ኮምፒውተሮችን በስጦታ አበርክቷል፡፡ ስጦታውን ያበረከቱት የሕብረት ባንክ ስትራቴጂና ቴክኖሎጂ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አንዷለም ኃይሉ ሕብረት ባንክ በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ገልጸው ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የሚደረገው ድጋፍም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
ድጋፉን የተቀበሉት የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ በበኩላቸው ሕብረት ባንክ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ከ28 አመታት በፊት የተቋቋመ ሀገር በቀል ግብረ-ሰናይ ድርጅት ሲሆን ሕብረት ባንክ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የአልማዝ ደረጃ አባል መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡
ሕብረት ባንክ