Mekedonia and Hibret 6

ሕብረት ባንክ ለሜቄዶኒያ የአዕምሮ ሕሙማንና አረጋውያን መርጃ ማዕከል የ6 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ::

ሕብረት ባንክ ለሜቄዶኒያ የአዕምሮ ሕሙማንና አረጋውያን መርጃ ማዕከል የ6 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ::

ሕብረት ባንክ በሜቄዶኒያ የሕብረት ባንክ ቀን ሆኖ በተሰየመው ጳጉሜ 4 ለሜቄዶኒያ የአዕምሮ ሕሙማንና አረጋውያን መርጃ ማዕከል አዲስ ዓመትን አስመልክቶ የ6 ሚሊየን ብር ስጦታ አበርክቷል፡፡

በድጋፍ ማድረግ መርሃግብሩ ላይ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አማካሪና ተወካይ የሆኑት አቶ ስምዖን አሰፋ  እንደተናገሩት ይህች ቀን በናፍቆት የምንጠበቃት በመሆንዋ ከባንኩ እና ከሰራተኛው ወርሃዊ ደምወዝ መዋጮ የተሰበሰበውን የገንዘብ ስጦታ ስናበረክት ደስታ ይሰማናል ብለዋል፡፡ አቶ ስምዖን አክለውም ሀገርን በብርቱ  ወጣትነትና የጎልማሳናት ጊዜያቸው ጉልበታቸውንና እውቀታቸውን ሳይሰስቱ ያገለገሉ ዜጎች አሁን ደግሞ ጉልበታቸው በደከመ ጊዜ ከጎናቸው በመቆም ድጋፍ በማድረጋችን  እንኮራለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የሜቄዶንያ መስራች የሆኑት ክቡር ዶ/ር ቢኒያም በለጠ በበኩላቸው ሕብረት ባንክና ሰራተኞቹ ላደረጉት ድጋፍና አስተዋፅኦ አመስግነው እየጨመረ ካለው የማዕከሉ ፍላጎት አንፃር ባንኩ ያደረገው ድጋፍ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የባንኩ የስራ አመራር አባላት በማዕከሉ የሚገኙ አረጋውያንና በመገንባት ላይ ሚገኘውን የማዕከሉን ሕንፃም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ 

ሕብረት ባንክ ለተለያዩ ድርጅቶች ድጋፍ በማድረግ ማሕበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን በሜቄዶንያ የሕብረት ቀን ሆኖ በተሰየመው ጳጉሜ 4 ቀን በመገኘት ድጋፍ ሲያደርግ ይህ ለአራተኛ ጊዜ ነው፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ! 

Similar Posts