ሕብረት ባንክ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ስልጠና ሰጠ

ሕብረት ባንክ ከ118 አፍሪካ ኤዚቲ ኢንፎርሜሽን ሰርቪስ ፒ.ኤል.ሲ. እና ከኢትዮጵያ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት ማህበር ጋር በመተባበር መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም በዋሽንግተን ሆቴል ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናው በፋይናንስና በጀት እንዲሁም በቁጠባና ብድር አሰጣጥ ላይ ያተኮረ ሲሆን ሰልጣኞቹ ደግሞ በአግሪ ቢዝነስ፤ በአገልግሎት እና ወጪ ንግድ ላይ የተሰማሩ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው፡፡

ሕብረት ባንክ እና 118 አፍሪካ ኤዚቲ ኢንፎርሜሽን ሰርቪስ ፒ.ኤል.ሲ. በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ጥር 3 ቀን 2015 ዓም በሕብረት ባንክ ዋና መሥርያ ቤት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts