Hibret Bank-Dashen Bank-02

ሕብረት ባንክ ለዳሸን ባንክ የ30ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱን አስተላልፏል::

ሕብረት ባንክ ለዳሸን ባንክ የ30ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱን አስተላልፏል::

የሕብረት ባንክ የቢዝነስ ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደረጀ ከበደ እና የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች በዳሸን ባንክ ዋና መ/ቤት በመገኘት ለ3ዐኛው ዓመት የዳሸን ባንክ  የምስረታ በዓል  የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በመልዕክታቸውም ሕብረት ባንክ እና ዳሸን ባንክ ለረጅም ጊዜ የቆየ የሥራ ትብብር ያላቸው አንጋፋ ባንኮች መሆናቸውን እና ይህ አጋርነትም ለፋይናንስ ዘርፉ ትልቅ እሴት እንደሆነ ገልፀው ለዳሸን ባንክ ረጅም ስኬታማ ዓመታትን ተመኝተዋል፡፡

የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይና የባንኩ ቺፍ ስትራቴጂ ኦፊሰር አቶ አየለ ተሾመ በበኩላቸው ሕብረት ባንክ ላስተላለፈው መልካም ምኞት እና የሁልጊዜ አጋርነት አመስግነው ወደፊትም ሁለቱ ባንኮች ያላቸውን ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡

በክብረ በዓሉ ላይ የሁለቱ ባንኮች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts