ሕብረት ባንክ ሕብር ሀቅ ለተሰኘው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱ የገበያ ቅስቀሳ መርሐ-ግብር አስጀመረ
ሕብረት ባንክ ሕብር ሀቅ ለተሰኘው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱ የገበያ ቅስቀሳ መርሐ-ግብር መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. የባንኩ የሼርአ አማካሪ ቦርዶች እና የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በሕብር ታወር በይፋ አስጀምሯል፡፡
ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የገበያ ቅስቀሳውን በይፋ ያስጀመሩት የባንኩ የስትራቴጂና ቴክኖሎጂ ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር አንዷለም ሀይሉ ሲሆኑ ሕብረት ባንክ የወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎትን በመስጠት ቀደሚ መሆኑን ገልፀው ባለፈው አሥር አመት ውስጥም ለሕብረተሰቡ በተቃና መልኩ ጥሩ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝና በዚህ በታላቁ የረመዷን ወር ጊዜም ይኼንኑ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ሕብር ሀቅ የገበያ ቅስቀሳ መርሐ-ግብር በባንኩ ሁሉም ቅርንጫፎች ከመጋቢት 6 እስክ ሚያዚያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ የሚቆይ ይሆናል፡፡
ሕብረት ባንክ!
በሕብረት እንደግ!!