ሕብረት ባንክ ሶስተኛውን ዙር የይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ ፣ይሸለሙ የሎተሪ የማውጣት መርሃ ግብር አከናወነ

ሕብረት ባንክ የሶስተኛው ዙር የይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ይሸለሙ ለባለዕድለኞች ዕጣ የማውጣት መርሐ-ግብር በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ መጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም. አካሄደ፡፡ ከነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ጥር 19 ቀን 2015 ዓ.ም. በባንኩ ለቆጠቡ፣ ከውጭ የተላከላቸውን የውጭ ምንዛሬ በባንኩ ለተቀበሉና ለመነዘሩ የባንኩ ደንበኞች በርካታ የተለያዩ የሽልማት አይነቶችን አዘጋጅቶ ዕጣ የማውጣት ሥነ-ሥርዓት ተከናውናል፡፡

ሎተሪ የማውጣት ሥነ-ሥርዓቱን በይፋ ያስጀመሩት የሕብረት ባንክ የስትራቴጂና ቴክኖሎጅ ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አንዷለም ኃይሉ ሲሆኑ በንግግራቸውም ሕብረት ባንክ ሲያካሂድ የቆየው የይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ይሸለሙ ፕሮግራም የደንበኞች የቁጠባ ባህላቸው እንዲዳብርና የውጭ ምንዛሪን በሕጋዊ መንገድ የመቀበል ባህላቸውን የሚያበረታታ ከመሆኑም በላይ የቤተሰባዊ ስሜትን ያጎለብታል ብለዋል፡፡

ዕጣ የማውጣት መርሐ-ግብሩ የሕብረት ባንክ የሥራ ኃላፊዎች፣ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ተወካዮችና ሠራተኞች እንዲሁም የሚዲያ ባለሙያዎች በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን ባለዕድለኞችን የቤት አውቶሞብል፣ ባለሦስት እግር ተሽከርካሪ፣ የውኃ ፓምፕ፣ ፍርጆች፣ የልብስ ማጠብያ ማሽኖች፣ ቴሌቭዥኖች፣ የውሃ ማጣሪያዎች እና የሞባይል ቀፎዎች አሸናፊ የሚያደርጋቸው ዕጣ ወቶላቸዋል፡፡

ሕብረት ባንክ ከዚህ በፊት በሁለት ዙር የይቆጥቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ ፣ይሸለሙ መርሐ-ግብር የሎተሪ ዕጣ አዘጋጅቶ ቃል በገባው መሠረት ለባለዕድለኞች መሸለሙ ይታወሳል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts