ሕብረት ባንክ በኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም 2026 ላይ እየተሳተፈ ይገኛል::
ሕብረት ባንክ በኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም 2026 ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
ሕብረት ባንክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባዘጋጀው ሁለተኛው የኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም 2026 ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
ፎረሙ በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም እየተካሄደ ሲሆን የመንግስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች፣ የኢንሹራንስ ድርጅት አመራሮች፣ እንዲሁም የተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ሃላፊዎች ታድመውበታል፡፡
ሕብረት ባንክ ከፎረሙ በተጨማሪ በተዘጋጀው ኤግዚቢሽን ላይ በልዩነት ያቀረባቸውን የፋይናንስ አገልግሎቶች በስፋት እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም 2026 እስከመስከረም 21 ቀን 2026 ዓ.ም. ድረስ የሚቆይ ይሆናል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!



