ሕብረት ባንክ እና ላኪፔይ ፋይናንሽያል ቴክኖሎጂስ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡





ሕብረት ባንክ እና ላኪፔይ ፋይናንሽያል ቴክኖሎጂስ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
ሕብረት ባንክ እና ላኪፔይ ፋይናንሽያል ቴክኖሎጂስ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም በሕብረት ባንክ ዋና መ/ቤት ተፈራርመዋል፡፡
በሕብረት ባንክ በኩል ስምምነቱን የፈረሙት የባንኩ የማርኬቲንግ እና ስትራቴጂ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ደረጀ ከበደ እንደተናገሩት ከውጪ ሀገር የሚላክ የውጭ ምንዛሬ በፈጣን ሲስተም ታግዞ ሕጋዊ በሆነ መንገድ ወደሀገራችን መድረስ መቻሉ ለባንኩ እና ለደንበኞች ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ለሀገር ኢኮኖሚ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልፀዋል፡፡ የላኪ ፔይ ፋይናንሽያል ቴክኖሎጂስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ታደሰ በበኩላቸው ሕብረት ባንክ እኛን መርጦ አብሮን በመስራቱ ደስታ ይሰማናል ብለዋል፡፡
በፊርማ ስነ-ሥርዓቱ ላይ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!