ሕብረት ባንክ እና አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

ሕብረት ባንክ እና አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የአጋርነት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ግንቦት 29 ቀን 2015 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ተፈራርመዋል፡፡

በሕብረት ባንክ በኩል ስምምነቱን የፈረሙት የሕብረት ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ከበደ እንዲህ አይነቱ ትብብር በጤናማ የውድድር መንፈስ ሲታገዝ ለባንኮች ሁለንተናዊ እድገት አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡ የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል ተከስተ በበኩላቸው ዛሬ የተጀመረው አጋርነት በቀጣይም በሌሎች ስራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

በሁለቱ ተቋማት መካከል የተደረሰው ስምምነት አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ላለመው የክራውድ ፈንዲንግ (crowd funding) ፕሮግራም የሕብረት ባንክን የ ኢ-ኮሜርስ ፕላትፎርም በመጠቀም በማስተር ካርድ በኩል ከውጭ ሀገር ገንዘብ ለማሰባሰብ የሚያስችል ነው፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts