ሕብረት ባንክ እና የአዲስ አበባ እድሮች ምክር ቤት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ
ሕብረት ባንክ እና የአዲስ አበባ እድሮች ምክር ቤት በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ግንቦት 03 ቀን 2015 ዓም በሕብረት ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ተፈራርመዋል፡፡
በሕብረት ባንክ በኩል ስምምነቱን የፈረሙት የባንኩ ስትራቴጂና ቴክኖሎጂ ም/ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አንዷለም ኃይሉ እንደገለፁት እድር ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ሀገራዊ እሴት በመሆኑ ባንኩ የአዲስ አበባ እድር ምክር ቤትን የማገዝ እድል በማግኘቱ ክብር ይሰማዋል፡፡
በአዲስ አበባ እድሮች ምክር ቤት በኩል ስምምነቱን የፈረሙት የአዲስ አበባ እድሮች ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ታምራት ገብረማርያም በበኩላቸው ሕብረት ባንክ እድሮችን ለማገዝ ፈቃደኛ የሆነ ቀዳሚ ባንክ መሆኑ አርአያነት ያለው ተግባር መሆኑን ጠቅሰው የተጀመረው አጋርነት ለውጤት እንደሚበቃ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል ፡፡
በሁለቱ ተቋማት መካከል የተደረሰው ስምምነት ስልታዊ አጋርነትን በመፍጠር ለእድሮች ምክር ቤት አባላት ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት የሚያግዝ ነው፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!