ሕብረት ባንክ እድሜያቸው ለጡረታ የደረሱ የማኔጅመንት አባላት የክብር ሽኝት አደረገ

ሕብረት ባንክ የስራ ዘመናቸውን አጠናቀው ለጡረታ ለደረሱት አቶ ጌቱ ገብረስላሴ፣ ኢንጂነር አክሊሉ ገብረኪዳን እና ኢንጂነር ግርማ ጥላዬ ሀምሌ 04 ቀን 2014 ዓ.ም. በዋናው መ/ቤት የምስጋናና የሽኝት መርሀግብር አካሂዷል፡፡

በምስጋናና በሽኝት መርሀግብሩ ላይ የተገኙት የሕብረት ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ከበደ ተመስጋኞቹ በስራ ዘመናቸው ለባንኩ ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነው ወደፊትም ቤተሰባዊነቱ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የስራ ዘመናቸውን አጠናቀው የተሸኙት ሰራተኞች ከባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ከበደ የምስጋና የምስክርነት ወረቀት የተቀበሉ ሲሆን ለተደረገላቸው የክብር ሽኝት አመስግነዋል ። በምስጋናና ሽኝት ኘሮግራሙ ላይ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

#HibretBank

Similar Posts