ሕብረት ባንክ ከሴንተር ፎር አክሰለሬትድ ዉሜንስ ኢኮኖሚክ ኢምፓወርመንት (CAWEE) ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ

ሕብረት ባንክ ከሴንተር ፎር አክሰለሬትድ ዊሜንስ ኢኮኖሚክ ኢምፓወርመንት ጋር አብሮ መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ሰኔ 14 ቀን 2015 ዓ.ም በባንኩ ዋና መስርያ ቤት ተፈራርሟል፡፡ የስምምነት ሰነዱን የፈረሙት የሕብረት ባንክ ስትራቴጂና ቴክኖሎጂ ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አንዷለም ሀይሉ እና የሴንተር ፎር አክሰለሬትድ ዉሜንስ ኢኮኖሚክ ኢምፓወርመንት መስራችና ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ንግስት ሀይሌ ናቸው፡፡

በስምምነት ሰነድ ፊርማ ሥነ-ስርዓቱ ወቅት የሕብረት ባንክ ስትራቴጂና ቴክኖሎጂ ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አንዷለም እንደገለፁት ሕብረት ባንክ የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የባንክ አገልግሎቶችን በማቅረብ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድም በትብብር ለጋራ ተጠቃሚነት መስራትን የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ወ/ሮ ንግስት ሀይሌ በበኩላቸው የስምምነት ሰነዱ መፈረም በዋናነት ባንኩ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ሴቶችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር መሆኑንና በአጋርነት አብሮ ለመስራት እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡

በፊርማ ስነ-ሥርዓቱ ላይ የሕብረት ባንክና የሴንተር ፎር አክሰለሬትድ ዉሜንስ ኢኮኖሚክ ኢምፓወርመንት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts