ሕብረት ባንክ ከተመራጭ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/መ/ህ/ስ/ማ ጋር በሲስተም ኢንተግሬሽን የተገበረውን የዲጂታል አገልግሎት አስጀመረ፡፡
ሕብረት ባንክ ከተመራጭ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/መ/ህ/ስ/ማ ጋር በሲስተም ኢንተግሬሽን የተገበረውን የዲጂታል አገልግሎት አስጀመረ፡፡
ሕብረት ባንክ የዲጂታል አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ከተለያዩ ተቋማት ጋር የጀመረውን ሥራ በመቀጠል አሁንም ከ7,200 በላይ አባላት ካሉት ከተመራጭ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/መ/ህ/ስ/ማሕበር ጋር የሲስተም ኢንተግሬሽን ፕሮጀክት በስኬት በማጠናቀቅ የማሕበሩ አባላት በሕብረት ሞባይል መተግበሪያ (Hibir Mobile App) በመታገዝ በቀላሉ ካሉበት ቦታ ሆነው በማንኛውም ጊዜ በሞባይል ባንኪንግ በቀጥታ ገንዘብ ለማስተላለፍ እና የሂሳብ እንቅስቃሴያቸውን ለማስተዳደር የሚችሉበትን አገልግሎት አስጀምሯል፡፡
ሁለቱ ተቋማት በተፈራረሙት የትብብር ስምምነት መሰረት ዘመናዊ የዲጂታል አገልግሎቶችን በስፋት ለማቅረብ እና ተቋማዊ የአሰራር ብቃትን ለመገንባት የጀመሩትን አጋርነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡
ሁለቱ ተቋማት በተፈራረሙት የትብብር ስምምነት መሰረት ዘመናዊ የዲጂታል አገልግሎቶችን በስፋት ለማቅረብ እና ተቋማዊ የአሰራር ብቃትን ለመገንባት የጀመሩትን አጋርነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!