ሕብረት ባንክ ከአይኤፍሲ (IFC) ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

ሕብረት ባንክና አለም አቀፉ የፋይናንስ ኮኦፐሬሽን አይኤፍሲ (International Finance Cooperation) በፋይናንስ አሰራሮች ዙርያ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ.ም በባንኩ ዋና መ/ቤት ተፈራርመዋል፡፡

በሕብረት ባንክ በኩል ስምምነቱን የፈረሙት የባንኩ ተ/ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ፅጌረዳ ተስፋዬ በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረገው ስምምነት ባንኩ የፋይናንስ፣ የሀብት አያያዝ እና የንብረት አስተዳደር ሥራዎችን በብቃት ለመከታተልና ለማካሄድ የሚረዳ ነው ብለዋል፡፡

የአይኤፍሲ የኢትዮጵያ፣ የዛሚቢያና ማላዊ ካንትሪ ማነጀር የሆኑት ማዳሎ ሚኖፉ (Madalo Minofu) በበኩላቸው ከሕብርት ጋር የተፈረመው ስምምነት የፋይናንስ ስራዎችን ለማጠናከር የሚረዳ መሆኑን ገልፀው በስምምነቱ መሰረት አይኤፍሲ ለሕብረት ባንክ የግምጃ ቤት፣ ሊኪዩዲቲ አስተዳደር (liquidity management) እንዲሁም አደጋዎችን የመቆጣጠርና ማስተዳደር ሥራዎችን ለማጠናከር ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡

በፊርማ ስነ-ሥርዓቱ ላይ የሕብረት ባንክና የአይኤፍሲ የስራ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts