Hibret-Bank-and-Ethio-Engineering-Group-MOU-1

ሕብረት ባንክ ከኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ::

ሕብረት ባንክ ከኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ::

ሕብረት ባንክ እና ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ሕዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም በሕብረት ባንክ ዋና መስርያ ቤት ተፈራርመዋል፡፡

በስምምነት ፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሕብረት ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ንጉሱ ገ/እግዚአብሔር ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ እንደ ሃገር ትልቅ ፋይዳ ያለውና ትሩፋቱም የጋራ መሆኑን ጠቅሰው ሕብረት ባንክ ከኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ጋር በጋራ በመስራቱ ደስታ ይሰማዋል ብለዋል፡፡ አቶ ንጉሱ አክለውም የሕብረት ባንክ ጥንካሬ የሚነሳው ከደንበኞቹ መሆኑንና የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕም ሕብረት ባንክ ታማኝ አጋር መሆኑን በማመን አብሮ ለመስራት መወሰኑ ለባንኩ ትልቅ አቅም እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡ በቀጣይ ሁለቱንም ተቋማት በሚጠቅም መልኩ የተደረሰውን ስምምነት ለመፈፀም ሕብረት ባንክ ዝግጁ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡

የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኮለኔል ሸጋው ሙሉጌታ በበኩላቸው ኢትዮ-ኢንጂነሪነግ ግሩፕ ከሕብረት ባንክ ጋር በአብሮነት ለመስራት ከስምምነት ላይ መደረሱ የጋራ ተጠቃሚነትን እንደሚፈጥር ገልፀው ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕም ለዚህ አጋርነት ስኬት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የሕብረት ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ንጉሱ ገ/እግዚአብሔርና የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኮለኔል ሸጋው ሙሉጌታ ሲሆኑ በስምምነት ፊርማው ስነ-ስርዓት ላይም የሕብረት ባንክና የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts