ሕብረት ባንክ የረመዷን ጾምን አስመልክቶ የኢፍጣር መርሃግብር አካሄደ።





ሕብረት ባንክ ታላቁን የረመዷን የጾም ወርን አስመልክቶ መጋቢት 6 ቀን 2017 ዓ.ም በወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን ቅጥር ግቢ ዉስጥ የኢፍጣር መርሃ ግብር አካሂዷል።
በኢፍጣር መርሃግብሩ ላይ የሕብረት ባንክ ተ/ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ፅጌረዳ ተስፋዬ እንደተናገሩት በታላቁ የረመዷን ጾም ወቅት የሚከወነው ኢፍጣር ቤተሰብን የሚያሰባስብና ሁሉም በሕብረት ማዕድ የሚቆርስበት፤ ያለው ለሌለው የሚያካፍልበትና አብሮነትንም የሚያጠናክርበት በመሆኑ ባንካችን በዘንድሮዉ ረመዷን የበጎ አድራጎት በሚሠራዉ በወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን የኢፍጣር መርሃግብር በማዘጋጀቱ ደስታ ይሰማዋል ብለዋል።
ወ/ሮ ፅጌረዳ አክለዉም ሕብረት ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን በሀገራችን በግንባር ቀደምነት ካስተዋወቁ ባንኮች አንዱ መሆኑንና በአሁኑ ወቅትም የሼሪዓውን መርህ በተከተለ መልኩ ሕብር ሀቅ በተሰኘዉ አገልግሎቱ በመላዉ ሀገሪቱ ባሉት ቅርንጫፎች አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
የፋውንዴሽኑ መስራች የሆኑት ወንድም ካሊድ በበኩላቸው ሕብረት ባንክ ይኸን የኢፍጣር መርሃግብር በማዘጋጀቱ አመስግነዋል።
የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የፕሬዘዳንት ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት ኡስታዝ አቡበከር በበኩላቸዉ ሕብረት ባንክ በተለየ መልኩ ከባንክ አገልግሎቱ ባሻገር በትክክለኛዉ ስፍራ በመገኘት ይኸን የኢፍጣር መርሃግብር በማዘጋጀቱ የሚያስመሰግነው ነው ብለዋል።
በመርሃግብሩ ላይ የባንኩ የሼሪዓ አማካሪ ቦርዶችና አመራሮች፣ የፋውንዴሽኑ የቦርድ አባላት፣የባንኩ ደንበኞችና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል።
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!