ሕብረት ባንክ የስኩል ሊደርሽፕ አካዳሚ ዎርክሾፕ አዘጋጀ
ሕብረት ባንክ ከኦፖርቹኒቲ ኢንተርናሽናል (Opportunity International) ጋር በመተባበር ስኩል ሊደርሽፕ አካዳሚ ኢኒሼቲቭ መርሆች ዙሪያ እና በሕብረት ባንክ በኩል የተዘጋጁ ለግል ትምህርት ቤት ባለቤቶች፣ መምህራን እና ሰራተኞች የሚሆኑ ሁለት አዳዲስ አገልግሎቶችን ለማስተዋወቅ ያለመ የሁለት ቀናት ወርክሾፕ በባንኩ ዋና መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ነሐሴ 7 እና 9 ቀን 2016 ዓ.ም አካሂዷል።
ለዎርክሾፑ ተሳታፊዎችም ሕብረት ባንክ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብርና ለትምህርት ቤቶችም ቴክኒካል ድጋፍ መስጠት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ገለፃ በመስጠት ከተሳታፊዎችም ለተነሱት ጥያቄዎች ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በዎርክሾፑ ማጠቃለያ ላይ የሕብረት ባንክና የኦፖርቹኒቲ ኢንተርናሽናል (Opportunity International) ተወካዮች በተገኙበት ስልጠናውን ላጠናቀቁ ትምህርት ቤቶች የምስክር ወረቀት ተበርክቷል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!!