ሕብረት ባንክ የተመሰረተበትን 25ኛ ዓመት አስመልክቶ ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

የሕብረት ባንክ  25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዮ ክብረ በዓል ከሕዳር 11 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡ የዚሁ በዓል አካል የሆነው የእውቅናና የድጋፍ መርሀ-ግብርም ሕዳር 13 ቀን 2016 ዓ/ም በሸራተን አዲስ ሆቴል አቶ ማሞ እስመለዓለም ምህረቱ የብሄራዊ ባንክ ገዥ፤ የሕብረት ባንክ መስራቾች፤ የባንኩ የቀድሞና የአሁን የቦርድ ሰብሳቢዎችና ዋና ስራ አስፈጻሚዎች እንዲሁም ለረዥም አመታት ያገለገሉ የባንኩ ሰራተኞችና ጥሪ የተደረገላቸው የባንኩ ደንበኞች በተገኙበት በድምቀት ተከናውኗል፡፡

በዚህ ዝግጅት ባንኩ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢነት  እና በዋና ስራ አስፈጻሚነት ያገለገሉ እንዲሁም አሁን በማገልገል ላይ ያሉ አመራሮች ከእለቱ የክብር እንግዳ  አቶ ማሞ እስመለዓለም ምህረቱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ እጅ እውቅና እና ሽልማት ተቀብለዋል፡፡ በተመሳሳይ ከ24 አመት እና ከዚያ በላይ በባንኩ ያገለገሉ ሰራተኞች ከባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ኢንጂነር ሳምራዊት ጌታመሳይ እጅ እውቅናና ሽልማት ተቀብለዋል፡፡

በተጨማሪም ለ10 የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ለእያንዳንዳቸው 1.5 ሚሊዮን ብር በድምሩ 15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡ ድጋፍ የተደረገላቸው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች መቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል፣ አወልያ እርዳታና ልማት ድርጅት፣ እዝነት የአካል ጉዳተኛ ህጻናትና ወላጆች መርጃ ድርጅት በኢትዮጵያ፣ ቢላሉል ሀበሺ የልማትና መረዳጃ ዕድር፣ ባቡል ኸይር በጎ አድራጎት ድርጅት፣ ይመለከተኛል በጎ አድራጎት ድርጅት፣ በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ፣ ሳሉ መረዳዳት የዐይነ ስዉራንና አካል ጉዳተኞች ማኅበር፣ የወደቁትን አንሱ የነዳያን መርጃ ማኅበር እና ጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማኅበር ናቸው፡፡

የሕብረት ባንክ 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ ክብረ-በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩን ይቀጥላል፡፡

ሕብረት ባንክ

በሕብረት እንደግ!

ድጋፍ የተደረገላቸው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች

መቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል፣

አወልያ እርዳታና ልማት ድርጅት፣

እዝነት የአካል ጉዳተኛ ህጻናትና ወላጆች መርጃ ድርጅት በኢትዮጵያ፣

ቢላሉል ሀበሺ የልማትና መረዳጃ ዕድር፣

ባቡል ኸይር በጎ አድራጎት ድርጅት፣

ይመለከተኛል በጎ አድራጎት ድርጅት፣

በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ፣

ሳሉ መረዳዳት የዐይነ ስዉራንና አካል ጉዳተኞች ማኅበር፣

የወደቁትን አንሱ የነዳያን መርጃ ማኅበር እና

ጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማኅበር ናቸው፡፡

Similar Posts