ሕብረት ባንክ የተቀማጭ ገንዘብ አገልግሎት የገበያ ቅስቀሳ መርሃግብር አዘጋጀ፡፡
ሕብረት ባንክ ለመላው ኢትዮጵያውያንና ለክቡራን ደንበኞቹ ከጥር 8ቀን እስከ መጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ የሚቆይ የተቀማጭ ገንዘብ አገልግሎት የገበያ ቅስቀሳ መርሃግብር አዘጋጅቷል፡፡ የገበያ ቅስቀሳ መርሃግብሩ ዋና አላማ ባንኩ የሚሰጣቸውን የተቀማጭ ገንዘብ አገልግሎቶችን ለማስተዋወቅ እና የደንበኞቹን ቁጥር የበለጠ ማሳደግ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ይህንኑ ለማሳካት ባንኩ አስራ ሶስት (13) አይነት ልዩ ወለድ እና ጥቅም የሚያስገኙ የተቀማጭ ገንዘብ አገልግሎቶችን አዘጋጅቶ ለደንበኞች አቅርቧል፡፡
የገበያ ቅስቀሳ መርሃ ግብሩን የሕብረት ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ከበደ በሕብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በሕብር ታወር ቅርንጫፍ መጀመሩን ሲያበስሩ የባንኩ ከፍተኛ የስራ አመራር አባላትም በእለቱ ተገኝተዋል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!