ሕብረት ባንክ የታማኝ ግብር ከፋይነት የፕላቲኒየም ደረጃ ሽልማት ተቀበለ

የ''ግብር ለሃገር ክብር" የግብር እና ታክስ ንቅናቄ አካል የሆነው 5ኛው ዙር የ2015 ዓ.ም የታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና መርሐ ግብር ጥቅምት 01/2016 ዓ.ም. በቤተመንግስት ተካሂዷል፡፡

ሕብረት ባንክም በአመቱ በታማኝ ግብር ከፋይነት የፕላቲንየም ደረጃ ሽልማት የተበረከተለት ሲሆን የባንኩ የቢዝነስና ኦፕሬሽንስ ሲኒየር ም/ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ጽጌረዳ ተስፋዬ ባንኩ ያገኘውን የታማኝ ግብር ከፋዮች ሽልማት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እጅ ተቀብለዋል፡፡

ሕብረት ባንክ የባንክ አግልግሎት በመስጠት ከሚያገኘው ገቢ ላይ በታማኝነት ግብር በመክፍል ሀገራዊ ግዴታውን እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን ሽልማቱም ለዚህ ተግባር እውቅና የሠጠ ነው፡፡

ሕብረት ባንክ

በሕብረት እንደግ!

Similar Posts