ሕብረት ባንክ የዘጠኝ ወር አፈፃፀም ግምገማውን አካሄደ፡፡






ሕብረት ባንክ የዘጠኝ ወር አፈፃፀም ግምገማውን አካሄደ፡፡
ሕብረት ባንክ የ2018 ዓ.ም የዘጠኝ ወር አፈፃፀም ግምገማውን በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት አዳራሽ ሚያዝያ 15 እና 16 ቀን 2018 ዓ.ም አካሂዷል፡፡
በተካሄደው የዘጠኝ ወር የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ እንደተገለፀው ባንኩ በዋና ዋና የአፈፃፀም መመዘኛዎች ላይ ጥሩ ውጤት አስመዝግቧል፡፡ ለተገኘው ውጤት በሁሉም ደረጃ የተቀናጀ ጥረት መደረጉ አስተዋፅኦ እንደነበረው የተገለፀ ሲሆን በቀጣይም ባንኩ በዓመቱ ያስቀመጠውን ዕቅድ ከግብ ለማድረስ ሁሉም የባንኩ ሰራተኛ ጠንክሮ መስራት እንዳለበት አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡
በስብሰባው ላይ ሕብረት ባንክ ባሻሻለው የ5 አመት የኮርፖሬት ስትራቴጂ እቅድ ላይ ገለፃ እና ውይይት የተደረገ ሲሆን በስትራቴጂው የተቀመጡትን ግቦች ለማሳካት መላው የባንኩ አመራርና ሰራተኛ በትብብርና በቅንጅት እንደሚሰራ ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
በዘጠኝ ወሩ የስራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ የባንኩ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትና የዲስትሪክት ዳይሬክተሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!