ሕብረት ባንክ የ25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ ክብረ በዓሉን ማብሰሪያ ፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ አካሄደ
ሕብረት ባንክ የ25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ ክብረ በዓል ማብሰሪያ ፕሮግራሙን የባንኩ የቦርድ አመራር አባላት፣ ማኔጅመንትና ሰራተኞች እንዲሁም የሚዲያ አካላት በተገኙበት ሕዳር 11 ቀን 2016 ዓ/ም በዋናው መስርያ ቤት ሕብር ታወር ሕንፃ አካሂዷል፡፡
ባንኩ የተጓዘው የሃያ አምስት ዓመታት የጉዞ ታሪክ የሁሉም የባንኩ መስራቾች፣ ባለአክሲዮኖች፣ ሠራተኞች፣ ደንበኞችና ባለድርሻ አካላት ታሪክ መሆኑ በማብሰርያ ፕሮግረሙ ላይ የተጠቀሰ ሲሆን ሩቅ አላሚ በሆኑ መስራቾች የተቋቋመው ሕብረት ባንክ በአካታችነቱ የሚታወቅ፤ በሕብረት ማደግን በተግባር ያስመሰከረ፣ሁሉንም የማሕበረሰብ ክፍል ማገልገል የቻለ እና በቴክኖሎጂ ልህቀት የተመሰከረለት የሁሉም ባንክ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በክብረ በዓሉ ላይ የ25ተኛ አመት የብር ኢዮቤልዩ መለያ ሎጎ ይፋ የተደረገ ሲሆን የባንኩን የሃያ አምስት አመታት ጉዞ የሚያሳይ የፎቶ ኤግዚቢሽንም በይፋ ተከፍቷል፡፡የፎቶ ኤግዚቢሽኑ ለ7 ተከታታይ ቀናት ለሕዝብ እይታ ክፍት ይሆናል፡፡
በማብሰርያ ፕሮግራሙ ወቅት የባንኩ 25ተኛ አመት የብር ኢዮቤልዩ ክብረ በዓል ለአንድ አመት በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከብር ሲሆን በዓሉንም አስመልክቶ በተቀመጡ መመዘኛዎች መሰረት ለተመረጡ አስር ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡
በሕብረት እንደግ!