ሕብረት ባንክ ያስገነባውን የዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ ሊያስመርቅ ነው

የሕብረት ባንክ አክሲዮን ማህበር ሰንጋ ተራ አካባቢ ያስገነባውን ባለ 37 ወለል የዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ “ሕብር ታወር” በሚል ስያሜ ቅዳሜ ጥር 7 ቀን 2014 ዓ.ም ያስመርቃል፡፡

በመዲናችንአዲስአበባ“የፋይናንስዲስትሪክት” የሚልስያሜንባገኘውናዋናዋናየፋናንስተቋማትበሚገኙበትሰንጋተራአካባቢ የተገነባው የሕብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ ለከተማዋ ልዩ ውበትን ያላበሰና ትልቅ አልሞ ትልቅ መድረስ እንደሚቻል በተግባር የታየበት ነው፡፡

ሕንጻው ዓለምአቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ ፋሲሊቲዎች ያሉት ሲሆን ዘመናዊ በ ኮምፓስ የሚሰሩ 13 አሳንሰሮች፤ በ ሴንሰር የሚሰራ መብራትና ዉሃ፤ ከ 147 በላይ ካሜራዎች፤ ባለ 270 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ዘመናዊ ስክሪን፤ የማያቋርጥ የሃይል አቅርቦት፤ BMS (Building Management System) የተገጠሙለት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለባንኩ ደንበኞች ባለ አራት ወለል በቂ የመኪና ማቆሚያ ቦታ ያለው ሲሆን በአጠቃላይ ሁለገብ እና የተሟላ ቀልጣፋ አግልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሕንፃ ነው፡፡

የሕብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ “ሕብር ታወር” ሶስት ብሎኮች አሉት፡፡ የመጀመሪያው G+4 ብሎክ ለተለያዩ የንግድ አገልግሎት ለሚሰጡድርጅቶችለኪራይየተዘጋጀሲሆን፣ሁለተኛውG+32ፎቅብሎክለተለያዩቢሮዎችየሚሆንነው፡፡ሶስተኛውG+4 የታወሩ ብሎክ ደግሞ የተለያየ መጠን ያላቸውን አዳራሾች፣ካፍቴሪያ፣ ዘመናዊ ኩሽናዎች እና ጂምናዚየምን አካትቷል፡፡ በዚህ በሶስተኛው ብሎክ ስር ያለው ዋና ነገር የባንኩ ሕብር ታወር ቅርንጫፍ ነው፡፡ ይህ ቅርንጫፍ ግዙፍ የውድ እቃዎች እና ዶክመንቶች ማስቀመጫ፣ እጅግ ዘመናዊ ቮልት፣ ለደንበኞች መስተንግዶ ቅልጥፍናና ምቾት የሚሰጥ ሰፊ ስፍራን ያካተተ ነው፡፡

በ2.8 ቢሊየን ብር ተገንብቶ የተጠናቀቀው የሕንፃው የግንባታ ሥራ በስድስት ዓመታት ውስጥ የተጠናቀቀ ሲሆን ዲዛይኑ ሀገር በቀል በሆነው የእስክንድር አርክቴክት ተሰርቶ ግንባታው ደግሞ በአለማችን በኮንትራክሽን ዘርፉ ተጠቃሽ በሆነው ቻይና ዢያንግሹ ኢንተርናሽናል(China Jiangsu International Economic Technical Cooperation Group LTD) ተከናውኗል፡፡

ሕብረት ባንክ ላለፉት 23 ዓመታት በዘመናዊ የባንክ አገለግሎት ፈር ቀዳጅ በመሆን የሀገራችንን ሕዝብ እያገለገለ የሚገኝ ባንክ ሲሆን የቅርንጫፍ ቁጥሩን ከ400 በላይ በማድረስ ለደንበኞች ተደራሽነቱን እያሰፋና ዘመናዊ ተክኖሎጂዎችን እያስተዋወቀ የሚገኝ አንጋፋ ባንክ ነው፡፡

Similar Posts