በአይነቱ ልዩ የሆነ የብድር አገልግሎት

ሕብረት ባንክ በጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ላይ ለተሰማሩ ወጣቶች፣ ሴቶችና አካል ጉዳተኞች በአይነቱ ልዩ የሆነ መጠነኛ የብድር አገልግሎት በዝቅተኛ የብድር ወለድ ምጣኔ እና በአነስተኛ ዋስትና እንዲሁም ለወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት አማራጭ ተጠቃሚ ለሆኑ ደንበኞቻችንም ይህንኑ አገልግሎት የሸሪዓ ህግጋቱን በጠበቀ መልኩ የምንሰጥ መሆኑን ስንገልፅ በደስታ ነው፡፡

የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች
» ኢትዮጵያዊ ዜጋ እና
» በዘርፉ ከ6 ወር በላይ የሰሩ መሆን አለባቸው
» የንግድ ፈቃድ ያላቸው

የአገልግሎቱ ፈላጊዎች ከአዲስ አበባ ውጭ በሁሉም የባንካችን ቅርንጫፎች በመገኘት የተዘጋጀውን ፎርም በመሙላት ወይም በተዘጋጀው ድረ-ገጽ www.Ethiomesmer.com ላይ በመመዝገብ የዕድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን።

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts