ንግድዎን መስመር እናስይዝልዎ!

ንግድዎን መስመር እናስይዝልዎ!
ሕብረት ባንክ በመስመር ብድር በሴቶች ባለቤትነት ስር ለሚተዳደሩ ጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ደረጃ ኢንተርፕራይዞች ልዩ የብድር አገልግሎት አዘጋጅቶ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾችን በመመዝገብ ላይ ይገኛል፡፡
የአካል ጉዳተኞች፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ከስደት ተመላሽ ሆነው በማኑፋክቸሪንግ እና በግብርና ዘርፍ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች፣ እንዲሁም ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ በሆኑ ሴቶች የሚመሩ ኢንተርፕራይዞች ልዩ ትኩረት ያገኛሉ፡፡
የዚህ ብድር ተጠቃሚ ለመሆን ከአዲስ አበባ ውጭ በሚገኙ የባንካችን ቅርንጫፎች በመቅረብ የተዘጋጀውን ማመልከቻ መሙላት ወይም Ethiomesmer.com ላይ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
አገልግሎቱን ለማግኘት መሟላት ያለባቸው:-
👉 ኢትዮጵያዊ ዜግነት
👉 የንግድ ፈቃድ ያላቸው
👉 በድርጅታቸው ውስጥ ሁለትና ከዚያ በላይ ሰራተኞች የሚያስተዳድሩ::
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!