Mekedonia-CSR-1

የሕብረት ባንክ ሠራተኞች ለሜቄዶንያ አረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል የ4 ሚልዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ፡፡

የሕብረት ባንክ ሠራተኞች ለሜቄዶንያ አረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን  መርጃ ማዕከል የ4 ሚልዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ፡፡

የሕብረት ባንክ ሠራተኞች ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም. ለመቄዶንያ አረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን  መርጃ ማዕከል ሁለተኛው ዙር የሕንፃ ማስጨረሻ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር የአራት ሚልዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገዋል፡፡ 

በመርሃ-ግብሩ ላይ የሕብረት ባንክ ኮርፖሬት ኮሚዩንኬሽን እና ኤቨንት ማኔጅመንት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሕይወት ዓለማየሁ ባስተላለፉት መልዕክት ጳጉሜ 4 የሕብረት ባንክ ቀን በመቄዶንያ ተብሎ በመሰየሙ ሕብረት ባንክና ሠራተኞቹ ኩራት እንደሚሰማቸው ገልጸው ባንኩ ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍል ባቀፈ መልኩ የላቀ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚተጋ እና ማሕበራዊ ሀላፊነቱንም በመወጣት ረጅም ርቀትን በሕብረት ለመጓዝ ትልቅ ራዕይ መሰነቁን አስታውቀዋል፡፡ ቀጥለውም  በመርሀ ግብሩ የተደረገው የ4 ሚልዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ መላው የባንኩ ሠራተኛ በየወሩ ለመቄዶንያ ከሚያዋጣው ገንዘብ የተሰበሰበ መሆኑን ገልጸው ባለፉት ዓመታትም ከ2ዐ ሚልዮን ብር  በላይ የገንዘብ ድጋፍ በሕብረት ባንክ እና በባንኩ ሠራተኞች  የተደረገ መሆኑን አስታውሰው ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡ 

የመቄዶንያ መስራች እና ባለራዕይ የሆኑት አቶ ቢንያም በለጠ በበኩላቸው የሕብረት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ፣ የሥራ አመራር አባላት እና ሠራተኞች እያደረጉት ያሉት ድጋፍ  ማዕከሉ እየሠራ ባለው ሰፊ ሥራ ላይ ትልቅ አሻራ እንዳለው በመግለጽ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ በመጨረሻም የሜቄዶንያ አባቶች መርሀ ግብሩን በምርቃት አሳርገዋል፡፡  

በመርሃ ግብሩ ላይ የባንኩ የሥራ አመራር አባላት ተገኝተዋል። 

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

Similar Posts