የሕብረት ባንክ የስራ አመራሮች አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

የአረንጓዴ አሻራ ሃገራዊ ራዕይን በመደገፍ የሕብረት ባንክ የስራ አመራሮች የአረንጓዴ አሻራ ማኖር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ነሐሴ 27 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባ አይሲቲ ፓርክ አካሂደዋል፡፡

የችግኝ ተከላው የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የአየር ጠባይን ለመቆጣጠር ብሎም ሀገራችንን የቱሪስት መስሕብ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደረግ ሲሆን ይህን መሰሉን መርሀ ግብር ባንኩ አጠናክሮ ለመቀጠል እንደሚሠራ ገልጿል፡፡

ባንኩ ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብሮችን ያካሄደ ሲሆን ይህም ማህበራዊ ሃላፊነቱን በመወጣት ረገድ እያበረከተ የሚገኘው አስተዋፅኦ አካል ነው፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

#አረንጓዴአሻራችን
#Hibretbank#Greenlegacy

Similar Posts