የአክሲዮን ሽያጭጨረታ ማስታወቂያ
ሕብረት ባንክ አ.ማ በባለአክሲዮኖች ተፈርመው ዋጋቸው ያልተከፈለባቸውን 1,301,424 (አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ አንድ ሺ አራት መቶ ሃያ አራት) አክሲዮኖችን ከዚህ በታች በተዘረዘረው አኳኋን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
- የአንዱ አክሲዮን የጨረታ መነሻ ዋጋ አንድ መቶ ብር(100.00) ሲሆን ተጫራቾች በመነሻው ዋጋ ላይ በተጨማሪ የሚከፍሉትን ፕሪሚየም ጨምረው የጨረታ ዋጋ መስጠት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች መጫረት የሚፈልጉትን የአክሲዮን ብዛት በአንድ መቶ ተባዝቶ የሚያገኙትን የብር መጠን ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ የክፍያ ማዘዣ/ሲ.ፒ.ኦ/ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የአክሲዮን ብዛትና ዋጋ ባንኩ ባዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ቅጽ በመሙላት፤የኢትዮጵያዊ ዜግነት ወይም የትውልደ ኢትዮጵያዊ ማስረጃ ኮፒ በማያያዝ፤ ከጨረታ ማስከበሪያው/ሲ.ፒ.ኦ./ ጋር በኤንቬሎፕ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ሥራ ኮሌጅ ፊትለፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሕብር ታወር ሕንጻ 24ኛ ፎቅ በሚገኘው የባንኩ ቺፍ ፋይናንስ ቢሮ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታው ማመልከቻ ቅጽ ከባንኩ ድህረ ገጽ(www. https://www.hibretbank.com.et/Share_Form) ወይንም ከባንኩ ፋይናንሻል አካውንቲንግ መምሪያ የአክሲዮን አስተዳደር ክፍል ወይንም ከባንኩ ቅርንጫፎች ማግኘት ይቻላል፡፡
- ጨረታው መስከረም 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡30 በሕብር ታወር ሕንጻ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የባንኩ ካፊቴሪያ ይከፈታል፡፡
- ለጨረታ የቀረቡት አክሲዮኖች ተሸጠው እስከሚጠናቀቁ ድረስ ከፍተኛ ዋጋ ያቀረቡ ተጫራቾች ከፍተኛ ዋጋ ካቀረበው ጀምሮ እንደቅደም ተከተላቸው አሸናፊ ይሆናሉ፡፡ ተጫራቾች የተጫረቱበትን ያህል አክሲዮኖች ባያገኙም መጨረሻ ላይ የሚተርፉትን አክሲዮኖች ባቀረቡት ዋጋ ለመግዛት ይገደዳሉ፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸውና ኢትዮጵያዊ ለመሆናቸው የሚያስረዳ የአገልግሎት ጊዜው ያላለፈበት መንጃ ፈቃድ፣ ፓስፖርት ወይም የቀበሌ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸውና የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያና ፓስፖርት ከጨረታው ጋር በኤንቬሎፕ ታሽጎ ሲቀርብ ሲሆን ዋናው በጨረታው መክፈቻ ዕለት መቅረብ አለበት፡፡ የሕግ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት ሙሉ ለሙሉ ኢትዮጵያዊ በሆኑ ባለአክሲዮኖች ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ ባለአክሲዮኖች የተቋቋመ እና የድርጅቱን መመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብ በጨረታው መክፈቻ ዕለት ማቅረብ የሚችሉ ከሆነ ነው፡፡
- በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ተጫራቾች ¼ ክፍያ ማስያዝ እንዲሁም ጨረታውን ካሸነፉ ክፍያ መፈፀም የሚቻለው ተቀባይነት ባለው የውጭ ምንዛሪ ብቻ ሲሆን በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሕብር ታወር ቅርንጫፍ በኩል ብቻ ይስተናገዳሉ፡፡
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ በ15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ለጨረታው ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ አክሲዮኖቹም በተከታታይ የመጫረቻ ዋጋ ላቀረቡ ተጫራቾች እንደጠየቁት መጠን የሚከፋፈል ሲሆን ፤ ይህ ካልሆነ ግን በድጋሚ ግልጽ ጨረታ በማውጣት ይሸጣሉ፡፡
- ሕጋዊ ሰውነት ባላቸው ድርጅቶች ስም የሚጫረቱ ወይም በውክልና ለሚጫረቱ በጨረታው ለመሳተፍ ግልጽ ስልጣን የሚሰጥ የተመዘገበ የውክልና ስልጣን ማስረጃ ዋናውን ተወካይ በጨረታው መክፈቻ ዕለት ማቅረብ አለበት፡፡
- ባንኩ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወጡ አግባብነት ያላቸው መመሪያዎችና ሌሎች ሕጎች ተፈጻሚነት አላቸው፡
- ከጨረታ ሰነዱ ጋር ኢትዮጵያዊ ዜግነት ወይም በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሚያሳይ ማስረጃ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. ተያይዞ ካልቀረበ የጨረታ ሰነዱ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ የባንኩን ፋይናንሻል አካውንቲንግ መምሪያ አክሲዮን አስተዳደር ክፍል በስልክ ቁጥር 0114-704932 እንዲሁም የሕግ አገልግሎት መምሪያ በስልክ ቁጥር 0114-700315/47 መጠየቅ ይቻላል፡፡