የጨረታ ማስታወቂያ – የጨረታ ቁጥር ሕብ/009/2016
ሕብረት ባንክ አ.ማ ለዋናው መስሪያ ቤት የጽዳት አገልግሎት ግዥ በዓመታዊ ውል በመግባት በጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከመጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ) በአካውንት ቁጥር IN0403007 አቅሪቢያችሁ በሚገኝ በማንኛውም የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ሰንጋ ተራ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ሕንፃ 19ኛ ፎቅ ግዥ ዋና ክፍል በመገኘት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ መምሪያው መሰረት የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን መመሪያ ያልተከተለ ተጫራቾች ከውድድር ሊታገዱ ይችላል፡፡
- እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡
- እያንዳንዱ ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ወይም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች እስከ ሚያዝያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 19ኛ ፎቅ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሚያዝያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከህብረት ባንክ ውጭ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበወ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114-67-32-08 ወይም 0114-70-65-41 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ሕብረት ባንክ አ.ማ